ኤልሳዕም፣ “በል እንግዲያው ጥራት” አለው፤ እርሱም ጠርቷት መጥታ በራፉ ላይ ቆመች።
ኤልሳዕም፣ “ታዲያ ምን ይደረግላት” ሲል ጠየቀ። ግያዝም፣ “ልጅ እኮ የላትም፤ ባሏም ሸምግሏል” አለ።
ኤልሳዕም፣ “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርሷም፣ “አይደለም ጌታዬ፣ አንተ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ ኋላ አገልጋይህን መዋሸት እንዳይሆንብህ!” አለችው።