ኢዮአቄምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ ልጁ ዮአኪንም በምትኩ ነገሠ።
በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ የፈጸመውም ድርጊት ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በርሱ ላይ ዘመተ፤ ወደ ባቢሎንም ይወስደው ዘንድ በናስ ሰንሰለት አሰረው።
በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባሩ የፈጸመው አስጸያፊ ድርጊትና በርሱ ላይ የተገኘበት ነገር ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። ልጁ ዮአኪንም በምትኩ ነገሠ።
“በሕያውነቴ እምላለሁ”፤ ይላል እግዚአብሔር “የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ የቀለበት ማኅተም ብትሆን እንኳ ኖሮ፣ አውልቄ እጥልሃለሁ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከዘሩ አይገኝም፤ ሬሳውም ወደ ውጭ ተጥሎ ለቀን ሐሩርና ለሌሊት ቍር ይጋለጣል።
“ስለ እስራኤል መሳፍንት ሙሾ አውጣ፤