ኢዮአካዝ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ሦስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ወር ገዛ። እናቱ አሚጣል ትባላለች፤ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። የእናቱም ስም አሚጣል ነበረ፤ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች፤ በኵሩ ዮሐናን፣ ሁለተኛ ልጁ ኢዮአቄም፣ ሦስተኛ ልጁ ሴዴቅያስ፣ አራተኛ ልጁ ሰሎም።
የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን ወስደው በአባቱ ምትክ በኢየሩሳሌም አነገሡት።
በአባቱ ምትክ በይሁዳ ላይ ስለ ነገሠው፣ ከዚህ ስፍራ በምርኮ ስለ ተወሰደው፣ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “ከእንግዲህ አይመለስም፤
ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም አሚጣል ነበረ፣ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።