ከዚያም ኢሳይያስ፣ “ትኵስ የበለስ ጥፍጥፍ አዘጋጁ” አላቸው፤ እነርሱም አዘጋጅተው ዕባጩ ላይ አደረጉለት፤ ተፈወሰም።
በዕድሜህም ላይ ዐሥራ ዐምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔ ስለ ራሴና ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስል ይህችን ከተማ እከላከልላታለሁ።’ ”
ሕዝቅያስም፣ “እግዚአብሔር እኔን ስለ መፈወሱ፣ ከሦስት ቀን በኋላም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ስለ መውጣቴ ምልክቱ ምንድን ነው?” ሲል ኢሳይያስን ጠየቀው።
ኤልሳዕም፣ “እስኪ ዱቄት አምጡልኝ” አለ። ያንም በምንቸቱ ውስጥ ጨምሮ፣ “እንዲመገቡት ለሰዎቹ አቅርቡላቸው” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ጕዳት የሚያስከትል ነገር አልተገኘም።
ኢሳይያስም፣ “የበለስ ጥፍጥፍ ወስዳችሁ በዕባጩ ላይ አድርጉለት፤ እርሱም ይፈወሳል” ብሎ ነበር።