ኤልሳዕ እንደ ተናገረውም ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ የተፈወሰ ነው።
ከዚያም ወደ ውሃው ምንጭ ሄዶ ጨው ጣለበትና “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን ውሃ ፈውሼዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለሞት ምክንያት አይሆንም፤ ምድሪቱንም ፍሬ እንዳትሰጥ አያደርጋትም’ አለ።”
ኤልሳዕም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድ ላይ ሲሄድ ሳለም ልጆች ከከተማ ወጥተው፣ “አንተ መላጣ፤ ውጣ! አንተ መላጣ ውጣ!” እያሉ አፌዙበት።