Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



2 ነገሥት 15:19

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም የአሦር ንጉሥ ፎሓ ምድሪቱን ወረረ፤ ምናሔም ርዳታውን ለማግኘትና በመንግሥቱ ላይ ያለውን ይዞታ ለማጽናት ሲል፣ አንድ ሺሕ መክሊት ብር ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስ ግን አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥ፣ ኢዮራም፣ አካዝያስ ለእግዚአብሔር ቀድሰው የለዩአቸውን የተቀደሱ ዕቃዎች በሙሉ፣ እርሱ ራሱ የቀደሳቸው ስጦታዎች እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤቶች የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ሰብስቦ ለሶርያ ንጉሥ ለአዛሄል ላከለት፤ አዛሄልም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።

መንግሥቱም በእጁ ከጸናለት በኋላ፣ ንጉሡን አባቱን የገደሉትን ሹማምት ገደላቸው።

በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ በዘመኑም ሁሉ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ካሳተበት ኀጢአት አልተመለሰም።

ምናሔም ገንዘቡ እንዲዋጣ ያደረገው ከእስራኤል ሲሆን፣ ይህንም ያደረገው ለአሦር ንጉሥ ይሰጥ ዘንድ እያንዳንዱ ሀብታም ዐምሳ፣ ዐምሳ ሰቅል ብር እንዲያዋጣ በማስገደድ ነበር። ስለዚህ የአሦር ንጉሥ በዚያች አገር አልቈየም፤ ተመልሶ ሄደ።

በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን፣ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮን፣ አቤልቤትመዓካን፣ ያኖዋን፣ ቃዴስንና አሦርን፣ ገለዓድንና ገሊላን፣ የንፍታሌምንም ምድር ጭምር ያዘ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ወደ አሦር ወሰደው።

አካዝም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤቶች የሚገኘውን ብርና ወርቅ ዘርፎ ለአሦር ንጉሥ ገጸ በረከት እንዲሆን ላከለት።

በዚህ ጊዜም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መዝጊያዎችና መቃኖች ላይ የለበጠውን ወርቅ ነቃቅሎ ለአሦር ንጉሥ ሰጠው።

“አሁንም አምላካችን ሆይ፤ ቃል ኪዳንህንና ዘላለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅ፣ ኀያልና የተፈራህ አምላክ ሆይ፤ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ፣ በነገሥታታችንና በመሪዎቻችን፣ በካህናታችንና በነቢያታችን፣ በአባቶቻችንና በመላው ሕዝብህ ላይ የደረሰው ይህ ሁሉ መከራ በፊትህ እንደ ቀላል ነገር አይታይ።

አሦርም ከእነርሱ ጋራ ተባበረ፤ የሎጥ ልጆችም ረዳት ሆነ። ሴላ

ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሰው የሚታመን፣ በሥጋ ለባሽ የሚመካ፣ ልቡንም ከእግዚአብሔር የሚያርቅ የተረገመ ነው።

“እስራኤል አንበሶች ያሳደዱት፣ የተበተነ መንጋ ነው፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ፣ ቦጫጭቆ በላው፤ በኋላም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣ ዐጥንቱን ቈረጣጠመው።”

“ኦሖላ የእኔ ሆና ሳለ በእኔ ላይ አመነዘረች፤ ጦረኞች ከሆኑት ጎረቤቶቿ ከአሦራውያን ውሽሞቿ ጋራ ሴሰነች፤

ለታላቁ ንጉሥ እንደ እጅ መንሻ፣ ወደ አሦር ይወሰዳል፤ ኤፍሬም ይዋረዳል፤ እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል።

“ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ፣ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ ቍስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች