በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር፣ የፈጸመው ሁሉና ያደረጋቸው ጦርነቶች እንዲሁም የይሁዳ ግዛት የነበሩትን ደማስቆንና ሐማትን እንዴት ለእስራኤል እንዳስመለሰ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?
ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።
ዳዊት የሱባን ኀይል በደመሰሰ ጊዜ፣ ሬዞን ሰዎቹን በዙሪያው አሰባስቦ የወንበዴ አለቃ ሆነ፤ ሰዎቹም ወደ ደማስቆ ሄደው ተቀመጡ፤ በዚያም አነገሡት።
የቀረው የኢዮርብዓም ታሪክ፣ ያደረገው ጦርነትና አገዛዙም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፏል።
ሌላው አካዝያስ በዘመኑ ያከናወናቸውና የፈጸማቸው ሥራዎች ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ የተጻፉ አይደለምን?
ዮአስ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በሰማርያም ከእስራኤል ነገሥታት ጋራ ተቀበረ፤ ልጁ ኢዮርብዓምም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
ኢዮርብዓም ከአባቶቹ ከእስራኤል ነገሥታት ጋራ አንቀላፋ፤ ልጁ ዘካርያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
እነዚህ ሁሉ በትውልድ መዝገብ የሰፈሩት በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአታምና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ነው።
የደማስቆን በሮች እሰባብራለሁ፤ በቤት ዔደን በትር የያዘውን፣ በአዌን ሸለቆ ያለውን ንጉሥ እደመስሳለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል” ይላል እግዚአብሔር።