Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



2 ነገሥት 12:8

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህናቱም ከእንግዲህ ከሕዝቡ ገንዘብ ላለመሰብሰብና ቤተ መቅደሱንም ራሳቸው ላለማደስ ተስማሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ ንጉሡ ኢዮአስ ካህኑን ዮዳሄንና ሌሎቹን ካህናት ጠርቶ፣ “በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን ያላደሳችሁት ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው፤ ቀጥሎም፣ “ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የፈረሰውን ለማደስ ይዋል እንጂ ከገንዘብ ያዦች አትቀበሉ” አላቸው።

ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ አንድ ሣጥን ወስዶ በመክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀለት፤ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚያስገባው በስተቀኝ በኩል በመሠዊያው አጠገብ አኖረው። በራፉን የሚጠብቁት ካህናትም ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣውን ገንዘብ በሙሉ በሣጥኑ ውስጥ ያስገቡ ነበር።

“ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኬልቅያስ ውጣ፤ የበር ጠባቂዎች ከሕዝቡ ሰብስበው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የገባው ገንዘብ ምን ያህል እንደ ሆነ ራሱ እንዲቈጥረው አድርግ፤

በንጉሡም ትእዛዝ የገንዘብ መሰብሰቢያ ሣጥን ሠርተው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግቢያ በር አጠገብ በውጭ በኩል አኖሩት።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች