በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጕድለት ያሟላል፤ የእነርሱም ደግሞ በተራው የእናንተን ጕድለት ያሟላል፤ በዚህም ያላችሁን እኩል ትካፈላላችሁ።
ከመካከላቸውም አንድ ችግረኛ አልነበረም፤ ምክንያቱም መሬትም ሆነ ቤት የነበራቸውን ሁሉ እየሸጡ ዋጋውን አምጥተው፣
ይህን የምንለው እናንተ ተቸግራችሁ ሌሎች ይድላቸው ለማለት ሳይሆን፣ ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ ነው።
ይህ የምትሰጡት አገልግሎት የቅዱሳንን ጕድለት የሚያሟላ ብቻ ሳይሆን፣ ብዙ ምስጋና ለእግዚአብሔር የሚቀርብበት ነው።