Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



2 ቆሮንቶስ 7:15

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደ ተቀበላችሁትና ሁላችሁም እንደ ታዘዛችሁ ሲያስታውስ ለእናንተ ያለው ፍቅር እየበረታ ሄዷል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴፍ ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ በጥልቅ ስለ ተነካ፣ ፈጥኖ ከፊታቸው ገለል አለ፤ ሰወር ያለ ቦታም ፈልጎ፣ ዕልፍኙ ውስጥ አለቀሰ።

በሕይወት ያለው ልጅ እናት ለልጇ እጅግ ስለ ራራች ንጉሡን፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለርሷ ስጣት፤ አትግደለው” አለች። ሌላዪቱ ግን፣ “ለእኔም ሆነ ለአንቺ አይሰጥም፤ ሁለት ላይ ይከፈል!” አለች።

ስለዚህ በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ በዘጠነኛው ወር በሃያኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ስለ ወቅቱ ጕዳይና ስለ ከባዱ ዝናብ በመጨነቅ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀምጠው ነበር።

በደል ከፈጸሙት ምርኮኞች የተነሣም በእስራኤል አምላክ ቃል የተንቀጠቀጡት ሁሉ በዙሪያዬ ተሰበሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥዋዕት ድረስ እጅግ እንደ ደነገጥሁ በዚያው ተቀመጥሁ።

ስለዚህ ነገር ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፤ ሰውነቴም በፍርሀት ይንቀጠቀጣል።

ሥጋዬ አንተን በመፍራት ይንቀጠቀጣል፤ ፍርድህንም እፈራለሁ።

እግዚአብሔርን በፍርሀት አገልግሉት፤ ለርሱ በመንቀጥቀጥ ደስ ያሰኛችሁ።

ውዴ እጁን በበሩ ቀዳዳ አሾለከ፤ ልቤም ስለ እርሱ ይታወክ ጀመር።

እነዚህን ነገሮች ሁሉ እጄ አልሠራችምን? እንዲገኙስ ያደረግሁ እኔ አይደለሁምን?” ይላል እግዚአብሔር። “ነገር ግን እኔ ወደዚህ፣ ትሑት ወደ ሆነና መንፈሱ ወደ ተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።

ኤፍሬም ሲናገር ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤ በእስራኤልም የተከበረ ነበር፤ ነገር ግን በኣልን ስላመለከ በደለ፤ ሞተም።

ሴት ቀኗ ደርሶ ስትወልድ ትጨነቃለች፤ ከተገላገለች በኋላ ግን፣ ሰው ወደ ዓለም ተወልዷልና ስለ ደስታዋ ጭንቋን ትረሳለች፤

የወህኒ ቤቱ ጠባቂም መብራት ለምኖ ወደ ውስጥ ዘልሎ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ እግር ላይ ወደቀ።

ወደ እናንተ የመጣሁት በድካምና በፍርሀት፣ እንዲሁም በብዙ መንቀጥቀጥ ነበር።

የጻፍሁላችሁም፣ የሚያጋጥማችሁን ፈተና መቋቋማችሁንና በሁሉም ነገር ታዛዦች መሆናችሁን ለማወቅ ነበር።

በእኛ አልተገደባችሁም፤ ነገር ግን በውስጣችሁ ተገድባችኋል።

ባሮች ሆይ፤ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ፣ በምድር ጌቶቻችሁ ለሆኑት በአክብሮትና በፍርሀት፣ በቅን ልብም ታዘዙ፤

በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ሁላችሁንም ምን ያህል እንደምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።

ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፤ ሁልጊዜም ታዛዦች እንደ ነበራችሁ ሁሉ፣ አሁንም እኔ በአጠገባችሁ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፣ ይልቁንም አሁን በሌለሁበት ጊዜ በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደ መሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤

በዚህ መልእክት ላይ ላለው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፣ እንደዚህ ያለውን ሰው በጥንቃቄ ተከታተሉት፤ በሥራውም እንዲያፍር ከርሱ ጋራ አትተባበሩ።

ማንም የዚህ ዓለም ሀብት እያለው፣ ወንድሙ ሲቸገር አይቶ ልቡ ባይራራለት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት በርሱ ይኖራል?




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች