ሰዎችን የሚኰንነው አገልግሎት የከበረ ከሆነ፣ የሚያጸድቀው አገልግሎት የቱን ያህል ይበልጥ የከበረ ይሆን!
ጽድቄን እያመጣሁ ነው፤ ሩቅም አይደለም፤ ማዳኔም አይዘገይም። ለጽዮን ድነትን፣ ለእስራኤል ክብሬን አጐናጽፋለሁ።
በርሱም ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ያለ ሥጋት ይኖራል፤ የሚጠራበትም ስም፣ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” የሚል ይሆናል።
ሳይገረዝ በነበረው እምነት ላገኘው ጽድቅ፣ የመገረዝን ምልክት ይኸውም የጽድቅን ማኅተም ተቀበለ፤ ስለዚህ ለሚያምኑ ነገር ግን ላልተገረዙት ጽድቅ ይቈጠርላቸው ዘንድ የሁሉ አባት ነው።
በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኗል።
የፀሓይ ክብር አንድ ዐይነት ነው፤ የጨረቃ ክብር ሌላ ነው፤ የከዋክብት ደግሞ ሌላ ነው፤ የአንዱም ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ክብር ይለያል።
ታዲያ፣ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ከዚያ የላቀ ክብር አይኖረውም?
እኛ በርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።
ሕግን በመጠበቅ የሚተማመኑ ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ የማያደርግ የተረገመ ነው” ተብሎ ተጽፏልና።
“የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።
ሕግ በመጠበቅ የሚገኝ የራሴ ጽድቅ ኖሮኝ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚመጣ፣ ከእምነትም በሆነ ጽድቅ በርሱ ዘንድ እንድገኝ ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ስምዖን ጴጥሮስ፤ በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በኩል እንደ ተቀበልነው ዐይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት፤