ነገር ግን አንድ ሰው ወደ ጌታ ዘወር ሲል መሸፈኛው ይወገዳል።
ሙሴም ከርሱ ጋራ ለመነጋገር ወደ እግዚአብሔር ሀልዎት በሚገባበት ጊዜ ሁሉ ግን፣ እስከሚወጣ ድረስ መሸፈኛውን ያነሣ ነበር፤ በወጣም ጊዜ የታዘዘውን ለእስራኤላውያን ነገራቸው።
በዚህም ተራራ ላይ፣ በሕዝብ ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣ በመንግሥታት ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል፤
በዚያ ጊዜ ደንቈሮ የጥቅልሉን መጽሐፍ ቃል ይሰማል፤ የዐይነ ስውሩም ዐይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ።
ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤ የልጆችሽም ሰላም ታላቅ ይሆናል።
ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤” ይላል እግዚአብሔር። “በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”
መንገዳችንን እንመርምር፤ እንፈትን፤ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።
እነርሱም ባለማመናቸው ጸንተው ባይኖሩ፣ ተመልሰው ይገባሉ፤ እግዚአብሔር መልሶ ሊያስገባቸው ይችላልና።
እስከ ዛሬም ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቍጥር መሸፈኛው ልቡናቸውን ይሸፍናል።
ይህም የሚሆነው፣ አምላክህን እግዚአብሔርን ከታዘዝህና በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዐቱን በመጠበቅ፣ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ስትመለስ ነው።
ስትጨነቅና ይህ ሁሉ ነገር ሲደርስብህ ያን ጊዜ፣ በኋለኞቹ ዘመናት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ትመለሳለህ፤ ትታዘዝለታለህም።