የሚያልፈው ያን ያህል ክብር ከነበረው፣ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም!
ከዚህ በፊት ክቡር የነበረው የላቀ ክብር ካለው ጋራ ሲወዳደር ክብር የሌለው ሆኗል።
እንግዲህ ይህን የመሰለ ተስፋ ስላለን፣ በድፍረት እንናገራለን።
ስለዚህ ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ይህ አገልግሎት ስላለን ተስፋ አንቈርጥም።
ይህን ኪዳን፣ “አዲስ” በማለቱ የፊተኛውን ኪዳን አሮጌ አድርጎታል፤ ስለዚህ ያረጀ ያፈጀው የሚጠፋበት ጊዜ ተቃርቧል።