ሰሎሞን አራት ሺሕ የፈረሶችና የሠረገሎች ጋጥ ነበረው፤ እንዲሁም ንጉሡ በሚኖርበት በኢየሩሳሌምና በሠረገላ ከተሞች ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት።
ሰሎሞን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺሕ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት፤ እነርሱንም በሠረገላ ከተሞችና ንጉሡ ባለበት በኢየሩሳሌም ከተማ አኖራቸው።
ሰሎሞን ሠረገላ የሚጐትቱ ፈረሶች የሚያድሩበት አራት ሺሕ ጋጣና ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት።
ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ የፈረሰኞችን ቍጥር ለመጨመር ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ እግዚአብሔር፣ “በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ” ብሏችኋልና።