ከዚያም ሰሎሞን በኤዶም ምድር የባሕር ጠረፍ ወደሚገኙት ወደ ዔጽዮንጋብርና ወደ ኤላት ሄደ።
ኢዮሣፍጥ ወርቅ ለማምጣት ወደ ኦፊር የሚሄዱ የተርሴስ መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ይሁን እንጂ በዔጽዮንጋብር ስለ ተሰበሩ ከቶ ወደዚያ መሄድ አልቻሉም ነበር።
ንጉሥ አሜስያስ ከአባቶቹ ጋራ ካንቀላፋ በኋላ ኤላትን እንደ ገና ሠርቶ ወደ ይሁዳ የመለሳት ይኸው ዓዛርያስ ነበር።
በዚያ ጊዜም የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የይሁዳን ሰዎች አሳድዶ፣ ኤላትን ወደ ሶርያ ግዛት መለሰ፤ ከዚያም ኤዶማውያን ወደ ኤላት መጥተው እስከ ዛሬ በዚያ ይኖራሉ።
ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦችን ለመሥራትም ተስማሙ፤ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር አሠሩ።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት ከተጣለበት ዕለት አንሥቶ እስከ ፍጻሜው ድረስ ያለው የሰሎሞን ሥራ ሁሉ ተከናወነለት፤ በዚሁ ሁኔታም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ከፍጻሜ ደረሰ።
ከዔብሮና ተነሥተው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ።
ስለዚህ በሴይር የሚኖሩ የዔሳው ዘሮች የሆኑ ወንድሞቻችንን ዐልፈናቸው ሄድን። ከኤላትና ከዔጽዮንጋብር ከሚመጣው ከዓረባ መንገድ ተመልሰን፣ በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ ተጓዝን።