ከዚያም ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት አቀረቡ።
ንጉሥ ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺሕ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺሕ በግና ፍየል ሠዋ፤ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ።
ገዥው በመካከላቸው በመሆን፣ ሲገቡ ይገባል፤ ሲወጡም ይወጣል።