ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና ቤተ መንግሥቱን ሠርቶ ከጨረሰና፤ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና ለራሱ ቤተ መንግሥት ያደርግ ዘንድ በልቡ ያሰበውን ሁሉ ካከናወነ በኋላ፣
ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ፣ ለራሱም ቤተ መንግሥት እንዲሠራ አዘዘ።
ሰሎሞንም በሰባተኛው ወር፣ በሃያ ሦስተኛው ቀን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ ሕዝቡን አሰናበተ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔር ለዳዊትና ለሰሎሞን እንዲሁም ለሕዝቡ ለእስራኤል ስላደረገው በጎ ነገር ሁሉ ከልብ ተደስተው ሐሤት እያደረጉ ወደ የቤታቸው ተመለሱ።
ታላላቅ ነገሮችን አከናወንሁ፤ ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፤ ወይንንም ተከልሁ፤