ጸሎትና ልመናቸውን በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ፍትሕንም አጐናጽፋቸው።
“ሕዝብህ ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ ወደምትልካቸው ቦታ ሁሉ በሚወጡበት ጊዜ፣ አንተ ወደ መረጥሃት ወደዚህች ከተማ፣ እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ወደ አንተ ቢጸልዩ፣
“መቼም ኀጢአት የማይሠራ ሰው የለምና ሕዝብህ በአንተ ላይ ኀጢአት ቢሠሩ፣ አንተም ተቈጥተህ ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ብትሰጣቸው፣ እነርሱም ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ የጠላት ምድር ቢጋዙ፣
ወፍረዋል፤ ሠብተዋልም። ክፋታቸው ገደብ የለውም፤ ወላጅ የሌላቸው ፍትሕ እንዲያገኙ አልቆሙላቸውም፤ ለድኾችም መብት አልተከራከሩም።