“አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት፣ ‘ልጆችህ አንተ እንደ አደረግኸው ሁሉ በሚያደርጉት ሁሉ ሕጌን በመጠበቅ በፊቴ ቢመላለሱ፣ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አታጣም’ ብለህ የሰጠኸውን ተስፋ አጽናለት።
እግዚአብሔርም፣ ‘ዘሮችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፣ እንዲሁም በፍጹም ልባቸው፣ በፍጹም ነፍሳቸው በታማኝነት በፊቴ ቢመላለሱ፣ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው ከዘርህ አላሳጣህም’ ሲል የሰጠኝን ተስፋ ይፈጽምልኛል።
“ስለምትሠራው ስለዚህ ቤተ መቅደስ ሥርዐቴን ብትከተል፣ ፍርዴን በተግባር ብትገልጸው፣ ትእዛዞቼን ብትጠብቅና ብትመላለስባቸው ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን ተስፋ በአንተ እፈጽመዋለሁ፤
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ዳዊትና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንዲነግሡ በጨው ኪዳን የሰጣቸው መሆኑን አታውቁምን?
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከዳዊት ጋራ ካደረገው ኪዳን የተነሣ፣ የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም መብራት እንደሚሰጥ ተስፋ ሰጥቶ ነበርና።
ጉባኤው ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ከንጉሡ ጋራ ቃል ኪዳን አደረጉ። ዮዳሄም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ለዳዊት ዘር በሰጠው ተስፋ መሠረት እነሆ፤ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል።
እንግዲህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ ለባሪያህ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም።
“አንተም አባትህ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ በፊቴ ብትሄድ፣ ያዘዝሁህን ሁሉ ብትፈጽም፣ ሥርዐቶቼንና ሕጎቼን ብትጠብቅ፣
ለአባትህ ለዳዊት፣ ‘እስራኤልን የሚገዛ ሰው ከዘርህ አታጣም’ በማለት በሰጠሁት ተስፋ መሠረት የመንግሥትህን ዙፋን አጸናለሁ።
ብፁዓን ናቸው፤ መንገዳቸው ነቀፋ የሌለበት፣ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ፤
ጕልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? በቃልህ መሠረት በመኖር ነው።
እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤ በማይታጠፍም ቃሉ እንዲህ አለ፤ “ከሆድህ ፍሬዎች አንዱን፣ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።
ወንዶች ልጆችህ ኪዳኔን፣ የማስተምራቸውንም ምስክርነቴን ቢጠብቁ፣ ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ፣ ለዘላለም ይቀመጣሉ።”
ምሕረትህ ከፊቴ አልተለየምና፣ በእውነትህም ተመላለስሁ።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እንደ ገና ለእስራኤል ቤት ልመና ዕሺ እላለሁ፤ ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ ሕዝባቸውን እንደ በግ መንጋ አበዛዋለሁ፤