የገንዳው ውፍረት አንድ ስንዝር ሲሆን፣ የከንፈሩ ጠርዝ ደግሞ የአበባ ቅርጽ ያለው የጽዋ ከንፈር የመሰለ ነው፤ ይህም ሦስት ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ ያህል ውሃ የሚይዝ ነው።
ገንዳውም፣ ሦስቱ ፊታቸውን ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ባዞሩ የዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስሎች ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ገንዳው በላያቸው ሆኖ የሁሉም የኋላ አካል በመካከል ላይ የገጠመ ነበር።
የገንዳው ውፍረት አንድ ስንዝር ሲሆን፣ የከንፈሩ ጠርዝ ደግሞ የአበባ ቅርጽ ያለው የጽዋ ከንፈር የመሰለ ነው፤ ይህም ሁለት ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ ያህል ውሃ የሚይዝ ነበር።
ዙሪያውንም አንድ ስንዝር ስፋት ያለው ጠርዝ አብጅለት፤ በጠርዙም ዙሪያ የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።