ገንዳውና ከሥሩ ያሉትን ዐሥራ ሁለት ኰርማዎች፤
መቆሚያዎች ከነመታጠቢያ ገንዳዎቻቸው፤
ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ሜንጦዎችንና ከእነዚሁም ጋራ የተያያዙ ዕቃዎች። ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር።