ሁለቱን አዕማድ፣ በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ሁለት ባለሳሕን ጕልላቶችን፤ በአዕማዱ ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ሁለት ጕልላቶችን ያስጌጡትን ሁለት መረቦች፤
ኪራም የእያንዳንዱ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ ዙሪያው ዐሥራ ሁለት ክንድ የሆነ፣ ሁለት የናስ ምሰሶዎች ሠራ።
ኪራምም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ። ኪራምም ለአምላክ ቤተ መቅደስ አገልግሎት ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራውን ሥራ ፈጸመ እነዚህም፦
በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ጕልላቶች የሚሸፍኑና በሁለት ረድፍ የተቀረጹትን መረቦች የሚያስጌጡትን አራት መቶ ሮማኖች፤