በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባሩ የፈጸመው አስጸያፊ ድርጊትና በርሱ ላይ የተገኘበት ነገር ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። ልጁ ዮአኪንም በምትኩ ነገሠ።
በአሜስያስ ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የተከናወነው ሌላው ተግባር ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
“በሕያውነቴ እምላለሁ”፤ ይላል እግዚአብሔር “የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ የቀለበት ማኅተም ብትሆን እንኳ ኖሮ፣ አውልቄ እጥልሃለሁ፤
ይህ ኢኮንያን የተባለ ሰው፣ የተናቀና የተሰበረ ገንቦ፣ ማንም የማይፈልገው ዕቃ ነውን? እርሱና ልጆቹ ለምን ወደ ውጪ ተጣሉ? ወደማያውቁትስ ምድር ለምን ተወረወሩ?