እኔን ትተውኝ ለሌሎች አማልክት ዕጣን ስላጠኑና በእጆቻቸው ሥራ ሁሉ ለቍጣ ስላነሣሡኝ፣ ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።’
እግዚአብሔርን ካለመታመናቸው የተነሣም፣ ሮብዓም በነገሠ በዐምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ።
እግዚአብሔርም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሸማያ መጣ፤ “ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ስላዋረዱ እታደጋቸዋለሁ እንጂ አላጠፋቸውም፤ ቍጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም።
እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋራ ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋራ ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን፣ ይተዋችኋል።
እነርሱም የአባቶቻቸውን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ትተው፣ የአሼራን ዐምዶችና ጣዖታትን አመለኩ፤ በበደላቸውም ምክንያት የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ መጣ።
እግዚአብሔርን እንድትጠይቁ ወደዚህ ቦታ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ እንዲህ በሉት፤ ስለ ሰማኸው ነገር የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
ነገር ግን አባቶቻችን የሰማይን አምላክ አስቈጥተውት ስለ ነበር፣ ለባቢሎኑ ንጉሥ ለከለዳዊው ናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ይህን ቤተ መቅደስ አፈራርሶ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን አፈለሰ።
ስለዚህ የሚነድድ ቍጣውን፣ የጦርነትንም መዓት አፈሰሰባቸው፤ በእሳት ነበልባል ከበባቸው፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን ልብ አላሉም።
ከዚያም፣ ‘የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ኪዳን ትተው ሌሎችን አማልክት ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው’ ይላሉ።”
እናንተ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፤ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤ አለዚያ ስለ ሠራችሁት ክፋት፣ ቍጣዬ እንደ እሳት ይንበለበላል፤ ሊገታውም የሚችል የለም።
“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ በሰውና በእንስሳ ላይ፣ በዱር ዛፍና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።
በጽኑ ቍጣው፣ የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ ሰበረ፤ ጠላት በተቃረበ ጊዜ፣ ቀኝ እጁን ወደ ኋላ መለሰ፤ በዙሪያው ያለውን ሁሉ እንደሚበላ እሳት፣ በያዕቆብ ላይ የእሳት ነበልባል ነደደ።
እንደ ጠላት ቀስቱን ገተረ፤ ቀኝ እጁ ተዘጋጅታለች፤ ለዐይን ደስ የሚያሰኙትን ሁሉ፤ እንደ ጠላት ዐረዳቸው፤ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ላይ፣ ቍጣውን እንደ እሳት አፈሰሰ።
እግዚአብሔር ለመቅሠፍቱ መውጫ በር ከፈተ፤ ጽኑ ቍጣውን አፈሰሰ፤ መሠረቷን እንዲበላ፣ በጽዮን እሳት ለኰሰ።
ሰው ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንዳነደድሁት ያያል፤ የሚያጠፋውም የለም።’ ”
ስለዚህ በምድሪቱ ላይ ደም ስላፈሰሱና በጣዖታቶቻቸው ስላረከሷት፣ መዓቴን አፈሰስሁባቸው።
እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ አለዚያ እንደ እሳት የዮሴፍን ቤት ያወድማል፤ እሳቱም ቤቴልን ይበላል፤ የሚያጠፋውም የለም።
ቍጣውን ማን ሊቋቋም ይችላል? ጽኑ ቍጣውንስ ማን ሊሸከም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሷል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጥቀዋል።