ሕዝቅያስና ሹማምቱም መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ሕዝቡን እስራኤልንም ባረኩ።
ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ሕዝቡን በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም ባረከ።
ከዚያም ቆሞ መላውን የእስራኤልን ጉባኤ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ ሲል መረቀ፤
ስጦታው በገዛ ፈቃድና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆቹ ለእግዚአብሔር ስላደረጉት የበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።
ይህንም በሦስተኛው ወር ጀምረው፣ በሰባተኛው ወር አጠናቀቁ።
ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ጠየቃቸው፤
መላው የእስራኤል ጉባኤ በዚያ ቆሞ ሳለ፣ ንጉሡ ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ ጉባኤውን ባረከ።
በኢየሩሳሌም የሚገኘው የእግዚአብሔር ቤት በዚህ ሁኔታ እንዲከበር ይህን በንጉሡ ልብ ያኖረ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን፤
ብፁዕ ነው፤ ይህ ባርኮት ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ፤ ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ።
ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነው ሕዝብ፣ ለርስቱ የመረጠውም ወገን፤
እኔ ለእናንተ ያለኝን በጎ ሐሳብ በቲቶ ልብ ውስጥ ያኖረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤
በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤
ብፁዕ ነህ፤ አንተ እስራኤል ሆይ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፣ እንደ አንተ ያለ ማን አለ? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፣ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ በፍርሀት ከፊትህ ያፈገፍጋሉ፤ አንተም የማምለኪያ ኰረብታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።”
ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደ አዲስ ስለ እኔ ማሰብ በመጀመራችሁ፣ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ በርግጥ በተግባር ለመግለጽ ዕድሉ አልነበራችሁም እንጂ ማሰቡንስ ታስቡልኝ ነበር።
አምላኬም እንደ ታላቅ ባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ይሞላባችኋል።
በእናንተ ምክንያት በአምላካችን ፊት ስላገኘነው ደስታ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምን ያህል ምስጋና ልናቀርብ እንችላለን?
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት፣
ልቤ ከእስራኤል መሳፍንት፣ ፈቃደኞችም ከሆኑ ሰዎች ጋራ ነው፤ እግዚአብሔር ይመስገን።