ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ በንግግሩ አበረታታ። በሰባቱም የቀን በዓል ቀናት እየበሉና የኅብረት መሥዋዕቱንም እያቀረቡ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
አሁንም ቢሆን አትፍሩ፤ ለእናንተና ለልጆቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” በማለት አረጋግጦ፣ በደግ ቃል አናገራቸው።
እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል።
እነርሱም የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በመሄድ በይሁዳ ሁሉ ላለው ሕዝብ አስተማሩ፤ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በመዘዋወርም ሕዝቡን አስተማሩ።
የጦር መኰንኖችንም በሕዝቡ ላይ ሾሞ በከተማዪቱ በር አደባባይ ላይ በፊቱ ከሰበሰበ በኋላ፣ እንዲህ ሲል አበረታታቸው፤
እስራኤልን ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩትና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አላቸው፤ “የእግዚአብሔርን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ አኑሩ፤ በእናንተ ትከሻ አትሸከሙት፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ።
አሁንም የአባቶቻችሁን አምላክ እግዚአብሔርን አክብሩ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ በዙሪያችሁ ካሉት አሕዛብና ከባዕዳን ሚስቶቻችሁ ተለዩ።”
ዕዝራ የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናትና በማድረግ፣ ለእስራኤልም ሥርዐቱንና ሕጉን በማስተማር ራሱን ፈጽሞ ሰጥቶ ነበር።
አንተም ዕዝራ ከአምላክህ እንደ ተሰጠህ ጥበብ መጠን፣ ከኤፍራጥስ ማዶ ለሚገኙት ሕዝቦች ሁሉ የአምላክህን ሕግ የሚያውቁ ዳኞችንና ፈራጆችን ሹምላቸው፤ ሕጉን የማያውቅ ሰው ቢኖር፣ አንተ ራስህ አስተምረው።
መልካሚቱ የአምላካችን እጅ በእኛ ላይ ስለ ነበረች፣ ከሞሖሊ ዘሮች የእስራኤል ልጅ የሌዊ ልጅ የሆነውን ሰራብያ ተብሎ የሚጠራውን አስተዋይ ሰው፣ ከርሱም ጋራ ዐሥራ ስምንት የሚሆኑ ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን፤
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ፣ ዕዝራ በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። እነርሱም በዓሉን ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛውም ቀን በሕጉ መሠረት የተቀደሰ ጉባኤ ተደረገ።
በያሉበትም ቦታ ቆመው ከአምላካቸው ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ሩብ ቀን አነበቡ፤ የቀረውን ሩብ ቀን ደግሞ ንስሓ በመግባትና ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር በመስገድ አሳለፉ።
የምናገረው ጠቃሚ ነገር ስላለኝ አድምጡኝ፤ ቀና ነገር ለመናገር ከንፈሮቼን እከፍታለሁ።
“ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤ በፍቅር ቃል አነጋግራታለሁ።
እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።
በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እግዚአብሔር የክብሩን ዕውቀት ብርሃን ይሰጠን ዘንድ፣ “በጨለማ ብርሃን ይብራ” ያለው እግዚአብሔር ብርሃኑን በልባችን አብርቷልና።
ሥርዐትህን ለያዕቆብ፣ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራል። ዕጣን በፊትህ፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በመሠዊያህ ላይ ያቀርባል።
ከዚህም በላይ ለርሱ ብዬ ሁሉን ነገር የተውሁለትን፣ ወደር የሌለውን ጌታዬን ክርስቶስ ኢየሱስን ከማወቅ ታላቅነት ጋራ ሳነጻጽር፣ ሁሉንም ነገር እንደ ጕድለት እቈጥረዋለሁ፤ ለርሱ ስል ሁሉን ዐጥቻለሁ፤ ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤
ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ዝግጁ ሁን፤ በታላቅ ትዕግሥትና በማስተማር አቅና፤ ገሥጽ፤ አበረታታም፤
ኢያሱም አካንን፣ “ልጄ ሆይ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጥ፤ ለርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውን ሳትደብቅ ንገረኝ” አለው።