እንደዚሁም የሁለተኛው ኪሩብ አንዱ ክንፍ ዐምስት ክንድ ሆኖ በአንጻሩ ያለውን የቤተ መቅደስ ግድግዳ ሲነካ፣ ዐምስት ክንድ የሆነው ሌላው ክንፉ ደግሞ የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።
ከዳር እስከ ዳር ገጥሞ የተዘረጋው የኪሩቤል ክንፍ በጠቅላላው ሃያ ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንዱ ክንፍ ዐምስት ክንድ ሆኖ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ሲነካ፣ ሌላው ዐምስት ክንድ የሆነው ክንፉ ደግሞ የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።
የተዘረጋው የእነዚህ ኪሩቤል ክንፍ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ፊታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል አዙረው በእግራቸው ቆመዋል።