የሰበሰቡንም በሮች ዘጉ፤ መብራቶቹንም አጠፉ። ለእስራኤል አምላክ ዕጣን አላጠኑም፤ በመቅደሱም የሚቃጠል መሥዋዕት አላቀረቡም።
አካዝ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃዎች ሁሉ አንድ ላይ ሰብስቦ ወሰደ፤ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሮች ዘጋ፤ በኢየሩሳሌምም በየአውራ ጐዳናው ማእዘን ላይ መሠዊያ አቆመ።
በዘመነ መንግሥቱ በመጀመሪያው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሮች ከፈተ፤ አደሳቸው።
“በየዕለቱ ያለ ማቋረጥ በመሠዊያው ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ ዓመት የሞላቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች፤
“አሮን መብራቶቹን በሚያዘጋጅበት ጊዜ፣ በየማለዳው ደስ የሚያሰኝ ሽታ ዕጣን በመሠዊያው ላይ ያጢስ።
“በመሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳት እንዳታነድዱ፣ ምነው ከእናንተ አንዱ የቤተ መቅደሱን ደጅ በዘጋ ኖሮ! እኔ በእናንተ ደስ አይለኝም፤ ከእጃችሁም ምንም ዐይነት ቍርባን አልቀበልም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።