ከዚያም እነዚሁ ሌዋውያን በሥራው ላይ ተሰማሩ፤ ከቀዓት ዘሮች የአማሢ ልጅ መሐትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮኤል፤ ከሜራሪ ዘሮች፣ የአብዲ ልጅ ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፤ ከጌርሶን ዘሮች፣ የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ዔድን፤
በስተ ግራቸው በኩል ዐብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጆች፤ የቂሳ ልጅ ኤታን፣ የአብዲ ልጅ፣ የማሎክ ልጅ፣
ከኤሊጻፋን ዘሮች፣ ሺምሪና ይዒኤል፤ ከአሳፍ ዘሮች፣ ዘካርያስና መታንያ፤
ይሒኤል፣ ዓዛዝያ፣ ናሖት፣ አሣሄል፣ ይሬሞት፣ ዮዛባት፣ ኤሊኤል፣ ሰማኪያ፣ መሐትና በናያስ በንጉሡ ሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ኀላፊ በዓዛርያስ ተሹመው በኮናንያና በወንድሙ በሰሜኢ ሥር ሆነው ተቈጣጣሪዎች ነበሩ።
ዔድን፣ ሚንያሚን፣ ኢያሱ፣ ሸማያ፣ አማርያና ሴኬንያ በካህናቱ ከተሞች ተገኝተው፣ ለካህናት ወገኖቻቸው ለታላላቆቹም ሆነ ለታናናሾቹ፣ እንደየምድባቸው፣ በማከፋፈሉ ረገድ በታማኝነት ረዱት።
የሌዊ ልጆች ስም ጌርሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ነው።