ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ልጁ አካዝም በምትኩ ነገሠ።
ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ አባቶቹ በተቀበሩበትም በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አካዝም በምትኩ ነገሠ።
በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ ኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ።
አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት ያደረገውን መልካም ነገር በእግዚአብሔር ፊት አላደረገም።