በእነዚህም የሚመራ ሦስት መቶ ሰባት ሺሕ ዐምስት መቶ ሰው ያለው ሰራዊት አለ፤ ይህም ንጉሡ በጠላቶቹ ላይ በሚያደርገው ዘመቻ ለመሰለፍ የሚበቃ ጠንካራ ኀይል ነበር።
ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ፣ የእስራኤልን ቤት ወግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም እንዲመልሱ ከይሁዳና ከብንያም ቤት አንድ መቶ ሰማንያ ሺሕ ወታደሮች ሰበሰበ።
ሮብዓም መንግሥቱን ከመሠረተና ካጸና በኋላ፣ እርሱና እስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ።
አብያ አራት መቶ ሺሕ ብርቱ ተዋጊዎች ይዞ ዘመተ፤ ኢዮርብዓምም ስምንት መቶ ሺሕ ብርቱ ተዋጊዎች ይዞ በመውጣት ጠበቀው።
እርሱም ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ አላቸው፤ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፤ ማማ፣ መዝጊያና መወርወሪያ ያላቸውን ቅጥሮች በዙሪያቸው እናብጅ። አምላካችንን እግዚአብሔርን ስለ ፈለግነው ምድሪቱ አሁንም የኛው ናት፤ እኛ ፈለግነው፤ እርሱም በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጠን” እነርሱም ሠሩ፤ ተከናወነላቸውም።
አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የያዙ ሦስት መቶ ሺሕ የይሁዳ ሰዎች እንዲሁም ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማንያ ሺሕ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ።
አሜስያስ የይሁዳን ሕዝብ በአንድነት ሰብስቦ፣ እንደየቤተ ሰቡ በሻለቆችና በመቶ አለቆች በመደልደል በመላው ይሁዳና በብንያም መደባቸው። ከዚያም ዕድሜያቸው ሃያና ከሃያ በላይ የሆናቸውን ሰብስቦ፣ ለውትድርና አገልግሎት ብቁ ሆነው ጋሻና ጦር መያዝ የሚችሉ ሦስት መቶ ሺሕ ሰዎች አገኘ።
በተዋጊዎቹ ላይ የተሾሙት የየቤተ ሰቡ መሪዎች ጠቅላላ ቍጥር ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ነበር።
ዖዝያን ለሰራዊቱ ሁሉ ጋሻ፣ ጦር፣ የራስ ቍር፣ ጥሩር፣ የቀስት ማስፈንጠሪያ ደጋንና የሚወነጨፍ ድንጋይ አደለ።