Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



2 ዜና መዋዕል 25:19

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ ኤዶምን አሸንፌአለሁ ብለህ ልብህ በትዕቢት ተወጥሯል፤ አሁን ክብርህን ጠብቀህ ዐርፈህ በቤትህ ተቀመጥ! ጠብ በመጫር በራስህና በይሁዳ ላይ ውድቀት ለማምጣት ችግር የምትፈጥረው ለምንድን ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የኤዶምን አማልክት ማምለክ በመፈለጋቸው፣ እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሊሰጣቸው ወስኗልና፣ አሜስያስ አልሰማም።

ዖዝያን ከበረታ በኋላ ግን ዕብሪቱ ለውድቀት ዳረገው። በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመግባቱ አምላኩን እግዚአብሔርን በደለ፤

የሕዝቅያስ ልብ ግን ታበየ እንጂ ስለ ተደረገለት በጎ ነገር ተገቢ ምላሽ አልሰጠም፤ በዚህ ምክንያት የእግዚአብሔር ቍጣ በርሱ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ።

ኒካዑ ግን መልእክተኛውን ልኮ፣ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፤ አንተንና እኔን የሚያጣላን ምንድን ነው? ጦርነት ከገጠምሁት ቤት ጋራ እንጂ በአሁኑ ጊዜ አንተን የምወጋህ አይደለሁም፤ እግዚአብሔር እንድፈጥን አዝዞኛል፤ ስለዚህ ከእኔ ጋራ ያለውን እግዚአብሔርን መቃወምህን ተው፤ አለዚያ ያጠፋሃል” አለው።

ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፤ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ትገኛለች።

ትዕቢት ጥፋትን፣ የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።

የሞኝ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤ አፉም በትር ይጋብዛል።

ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤ ቂል ሁሉ ግን ለጥል ይቸኵላል።

በሌሎች ጠብ ጥልቅ የሚል መንገደኛ፣ የውሻ ጆሮ እንደሚይዝ ሰው ነው።

ሥሥታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል።

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበበኛ በጥበቡ አይታበይ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይኵራራ፤

የደቡቡ ንጉሥ ብዙ ሰራዊት በሚማርክበት ጊዜ ልቡ በትዕቢት ይሞላል፤ በብዙ ሺሕ የሚቈጠሩ ሰዎችንም ይገድላል፤ ነገር ግን በድል አድራጊነቱ አይጸናም።

“እነሆ፤ እርሱ ታብዮአል፤ ምኞቱ ቀና አይደለም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ ይኖራል።

“ወይም አንድ ንጉሥ ከሌላው ንጉሥ ጋራ ጦርነት ሊገጥም በሚነሣበት ጊዜ፣ ሃያ ሺሕ ሰራዊት አስከትቶ የሚመጣበትን ንጉሥ፣ በዐሥር ሺሕ ሰራዊት መመከት እንደሚችል ተቀምጦ የማይመክር ማን ነው?

ይኸውም ሥጋ ለባሽ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ ነው።

ልብህ ይታበይና ከባርነት ምድር፣ ከግብጽ ያወጣህን አምላክህን እግዚአብሔርን ትረሳለህ።

ነገር ግን ጸጋን አብዝቶ ይሰጠናል፤ መጽሐፍም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ያለው ስለዚህ ነው።

ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች