አሜስያስም ኀይሉን በሚገባ አደራጅቶ ሰራዊቱን ወደ ጨው ሸለቆ መራ፤ በዚያም ዐሥር ሺሕ የሴይር ወታደሮችን ገደለ።
ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ኤዶማውያንን ገድሎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ።
የጨው ሸለቆ በተባለው ቦታ ዐሥር ሺሕ ኤዶማውያንን ድል ያደረገ፣ ሴላን በጦርነት የያዘና እስከ ዛሬም ድረስ ዮቅትኤል ተብላ የምትጠራበትን ስም ያወጣላት አሜስያስ ነው።
ስለዚህ አሜስያስ ከኤፍሬም ወደ እርሱ የመጡትን ወታደሮች ወደየመኖሪያ ስፍራቸው አሰናበታቸው። እነርሱም በይሁዳ ላይ ክፉኛ ተበሳጭተው ነበርና በታላቅ ቍጣ ወደ መኖሪያ ስፍራቸው ተመለሱ።
የይሁዳ ሰራዊት ሌሎች ዐሥር ሺሕ ሰዎች ማረኩ፤ ወደ አንድ ዐለት ዐናት ላይም አውጥተው ቍልቍል ለቀቋቸው፤ ሁሉም ተፈጠፈጡ።
የእግዚአብሔርም ቍጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ፤ ነቢይንም ላከበት፤ ነቢዩም፣ “የገዛ ሕዝባቸውን ከእጅህ ማዳን ያልቻሉትን የአሕዛብን አማልክት ርዳታ የጠየቅኸው ለምንድን ነው?” አለው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጣልኸን፤ አንኰታኰትኸን፤ ተቈጣኸንም፤ አሁን ግን መልሰህ አብጀን።
አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥ የምትኖር፣ መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ ለራስህም፣ ‘ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?’ የምትል፣ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።