Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



2 ዜና መዋዕል 23:8

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሌዋውያኑና ይሁዳ ሁሉ ልክ ካህኑ ዮዳሄ እንዳዘዘው አደረጉ፤ ካህኑ ዮዳሄ ከጥበቃ ክፍሎች የትኛውንም አላሰናበተም ነበርና፣ እያንዳንዱ በሰንበት ቀን በሥራ ላይ የሚሰማሩትንና ከሥራ የሚወጡትን የራሱን ሰዎች ወሰደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የመቶ አለቆቹም ልክ ካህኑ ዮዳሄ እንዳዘዘው አደረጉ፤ እያንዳንዳቸውም በሰንበት ዕለት ለዘብ ጥበቃ የሚገቡትንና ከዘብ ጥበቃ የሚወጡትን ጭፍሮቻቸውን ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ።

ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተ ሰቡ ኀላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዛዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች ነበሩ።

ወንድሞቻቸውም በየመንደሮቻቸው ሆነው በየጊዜው እየወጡ የጥበቃውን ሥራ ሰባት ሰባት ቀን ያግዟቸው ነበር።

ሌዋውያኑም እያንዳንዱ የጦር መሣሪያውን በእጁ ይዞ በንጉሡ ዙሪያ ሁኑ፤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚገባ ማንም ሰው ይገደል፤ ንጉሡ በሚሄድበትም ቦታ ሁሉ ዐብራችሁት ሁኑ።”

ካህኑ ዮዳሄ በአምላክ ቤተ መቅደስ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮች፣ ትላልቅና ትናንሽ ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች