የቀረውም ኢዮሣፍጥ በዘመነ መንግሥቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ያከናወናቸው ተግባራት፦ የአናኒ ልጅ ኢዩ በዘገበው የእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቧል።
የቀረው የኢዮርብዓም ታሪክ፣ ያደረገው ጦርነትና አገዛዙም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፏል።
ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል በባኦስ ላይ እንዲህ ሲል ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ፤
በዚህ ሁኔታም በነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ በተነገረው በእግዚአብሔር ቃል መሠረት፣ የባኦስን ቤተ ሰብ ሁሉ ፈጀ።
ከዚህም በቀር የእግዚአብሔር ቃል በአናኒ ልጅ፣ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባኦስና በቤቱ ላይ የመጣበት ምክንያት፣ በእጁ ሥራ ያስቈጣው ዘንድ እንደ ኢዮርብዓም ቤት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራን ሁሉ በማድረጉና ኢዮርብዓምን በማጥፋቱም ጭምር ነው።
የቀረውም ኢዮሣፍጥ በዘመነ መንግሥቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ያከናወናቸው ተግባራት፦ ጀግንነቱና ያደረጋቸው ጦርነቶች ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፉ አይሉምን?
ሮብዓም በዘመነ መንግሥቱ ያከናወናቸው ተግባሮች ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ነቢዩ ሸማያ በጻፈው የታሪክ መዝገብና ባለራእዩ አዶ በዘገበው የትውልድ ሐረግ ታሪክ የሚገኝ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር።
በአብያ ዘመን የተከናወነው ተግባር፣ እርሱ የፈጸመውና የተናገረው ሁሉ በነቢዩ በአዶ የታሪክ መዛግብት ተጽፏል።
በአሳ ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወነው ሥራ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጻሕፍት ተጽፏል።
በዚያ ጊዜም ባለራእዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ሳይሆን በሶርያ ንጉሥ ስለ ታመንህ፣ የሶርያ ንጉሥ ሰራዊት ከእጅህ አምልጧል።
ባለራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሥ ኢዮሣፍጥንም እንዲህ አለው፣ “አንተ ክፉውን መርዳትህና እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ማፍቀርህ ተገቢ ነውን? ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ ባንተ ላይ ነው፤
በአሜስያስ ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የተከናወነው ሌላው ተግባር ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?