ኢዮሣፍጥ በይሁዳ ነገሠ። መንገሥ በጀመረ ጊዜም ዕድሜው ሠላሳ ዐምስት ዓመት ሲሆን፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ሃያ ዐምስት ዓመት ገዛ። እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች።
እርሱም በአካሄዱ ሁሉ የአባቱን የአሳን መንገድ ተከተለ፤ ከዚያም ፈቀቅ አላለም፤ በእግዚአብሔርም ፊት መልካም የሆነውን አደረገ፤