2 ዜና መዋዕል 2:14አዲሱ መደበኛ ትርጒምእርሱም እናቱ ከዳን ወገን፣ አባቱም የጢሮስ አገር ሰው ነው፤ በወርቅና በብር፣ በናስና በብረት፣ በድንጋይና በዕንጨት፤ እንዲሁም በሐምራዊና በሰማያዊ፣ በቀይ ግምጃና በቀጭን በፍታ ሥራ የሠለጠነ ሲሆን፣ በልዩ ልዩ ቅርጻ ቅርጽ ሥራ ልምድ ያካበተና የተሰጠውን ማንኛውንም ንድፍ በሥራ መተርጐም የሚችል ባለሙያ ነው። እርሱም ከአንተ የእጅ ሥራ ባለሙያዎችና ከጌታዬ ከዳዊት የእጅ ሥራ ባለሙያዎች ጋራ ዐብሮ ይሠራል። ምዕራፉን ተመልከት |