ይሁን እንጂ የአሼራን ዐምዶች ከምድሪቱ ስላስወገድህና እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልብህን ስላዘጋጀህ፣ መልካም ነገር ተገኝቶብሃል”።
እስራኤልም ሁሉ አልቅሰው ይቀብሩታል። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከኢዮርብዓም ቤት ሁሉ መልካም ነገር ያገኘበት እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፣ በወግ በማዕርግ የሚቀበር እርሱ ብቻ ነው።
ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ ከልባቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፣ ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ።
ሮብዓም ራሱን ዝቅ አድርጎ ስላዋረደ፣ የእግዚአብሔር ቍጣ ከርሱ ተመለሰ፤ ፈጽሞም አላጠፋውም። በይሁዳም ደግሞ በጥቂቱም ቢሆን መልካም ነገር ተገኝቶ ነበር።
እግዚአብሔርን ይሻ ዘንድ ልቡን ስላላዘጋጀ ክፉ ነገር አደረገ።
የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ።
በፍጹም ልባቸው ስለ ማሉም የይሁዳ ሕዝብ በመሐላው ደስ ተሠኙ። እግዚአብሔርን ከልብ ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጣቸው።
ኢዮሣፍጥም እጅግ ስለ ፈራ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም ዐወጀ።
ይሁን እንጂ በየኰረብታው ላይ ያሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ገና አልተወገዱም፤ ሕዝቡም ገና ልቡን በአባቶቹ አምላክ ላይ አላደረገም ነበር።
ከዚያም አካዝያስን ለመፈለግ ሄደ፤ የእርሱም ሰዎች አካዝያስን በሰማርያ ከተደበቀበት አግኝተው ያዙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት። “እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው” በማለት ቀበሩት። ስለዚህ ከአካዝያስ ቤት የመንግሥቱን ሥልጣን ይይዝ ዘንድ የሚችል ሰው አልነበረም።
ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት ስለ ተመላለሰ፣ እየበረታ ሄደ።
ምንም እንኳ በመቅደሱ ሥርዐት መሠረት የነጹ ሆነው ባይገኙም፣ የአባቶቻቸው አምላክ የሆነውን እግዚአብሔር አምላካቸውን ለመፈለግ ልባቸውን የሚያዘጋጁትን ሁሉ ይቅር በላቸው።”
ዕዝራ የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናትና በማድረግ፣ ለእስራኤልም ሥርዐቱንና ሕጉን በማስተማር ራሱን ፈጽሞ ሰጥቶ ነበር።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ እቀኛለሁ፤ እዘምራለሁ።
በእኔ፣ ማለትም ኀጢአተኛ በሆነው ተፈጥሮዬ ውስጥ ምንም በጎ ነገር እንደማይኖር ዐውቃለሁ፤ በጎ የሆነውን የማድረግ ምኞት አለኝ፤ ነገር ግን ልፈጽመው አልችልም።
ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፣ “በፍጹም ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱ ከሆነ፣ ሌሎችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ራሳችሁንም ለእግዚአብሔር አሳልፋችሁ ስጡ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋችኋል።” አላቸው።