ቀጥሎም ዮዛባት ለጦርነት ዝግጁ ከሆኑ ከአንድ መቶ ሰማንያ ሺሕ ሰዎች ጋራ።
እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ ዐሥራ ሰባት ሺሕ ተዋጊዎች ነበሯቸው።
ከብንያምም ጀግናው ወታደር ኤሊዳሄ ቀስትና ጋሻ ከያዙ ከሁለት መቶ ሺሕ ሰዎች ጋራ፤
እነዚህ እንግዲህ በመላው ይሁዳ በተመሸጉት ከተሞች ካስቀመጣቸው ሌላ፣ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው።