እንዲህም አላቸው፤ “ ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች የምትሰጡኝ ምክር ምንድን ነው? ምንስ ብለን እንመልስላቸው?”
ዐብሮ አደጎቹም ወጣቶች እንዲህ አሉት፤ “ ‘አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚሉህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤
ከዚያም ንጉሡ ሮብዓም አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ ካገለገሉት ሽማግሌዎች ጋራ ተማከረ፤ “ለዚህ ሕዝብ ምን መልስ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” አላቸው።
ሮብዓም ግን ሽማግሌዎች የሰጡትን ምክር ንቆ፣ ዐብሮ አደጎቹና አገልጋዮቹ ከሆኑት ወጣቶች ምክር ጠየቀ፤