ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ወዳለው ወደ ናሱ መሠዊያ ወጥቶ በላዩ ላይ አንድ ሺሕ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።
ከሁሉ የሚበልጠው የማምለኪያ ኰረብታ ገባዖን ስለ ነበረ፣ ንጉሡ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ። ሰሎሞን በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺሕ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።
ንጉሥ ሰሎሞንና ዐብሮት በዚያ የተሰበሰበው መላው የእስራኤል ጉባኤ በታቦቱ ፊት ስፍር ቍጥር የሌላቸውን በጎችና በሬዎች ሠዉ።
ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺሕ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺሕ በግና ፍየል የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ንጉሡና እስራኤላውያንም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ።
በማግስቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠዉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም አቀረቡ፤ ይህም አንድ ሺሕ ወይፈን፣ አንድ ሺሕ አውራ በግ፣ አንድ ሺሕ የበግ ጠቦት ሲሆን፣ ከመጠጥ ቍርባኖቻቸውና ከሌሎች መሥዋዕቶች ጋራ ስለ እስራኤል ሁሉ በብዛት አቀረቡ።
ሰሎሞንም በቤተ መቅደሱ መመላለሻ ፊት ለፊት ባሠራው የእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ።
ሊባኖስ ለመሠዊያ እሳት አትበቃም፤ የእንስሶቿም ቍጥር ለሚቃጠል መሥዋዕት ያንሳል።