ማንም በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁልጊዜ መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።
ከዚህ በኋላ ወንድሞቹን አሰናበታቸው፤ ከርሱም ሲሰናበቱ፣ “መንገድ ላይ እንዳትጣሉ!” አላቸው።
መልካሙን ስለ ተከተልሁ፣ በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ ከሰሱኝ።
በጎ ለዋለልኝ ክፉ መልሼ ብሆን፣ ጠላቴንም በከንቱ ዘርፌ ከሆነ፣
በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልስ ሰው፣ ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።
“ለደረሰብኝ በደል ብድሬን ባልመልስ!” አትበል፤ እግዚአብሔርን ጠብቅ፤ እርሱ ይታደግሃል።
ጠላትህ ሲወድቅ ደስ አይበልህ፤ ሲሰናከልም ልብህ ሐሤት አያድርግ፤
“በእኔ ላይ እንደ ሠራብኝ እሠራለታለሁ፤ ስለ አድራጎቱም የእጁን እመልስለታለሁ” አትበል።
ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም ውሃ አጠጣው።
“ ‘ወገንህን አትበቀል፤ ወይም በመካከልህ ከሚኖር በማንኛውም ሰው ላይ ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ‘ክፉ አድራጊውን ሰው አትቃወሙት’፤ ነገር ግን ቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጕንጭህን ደግሞ አዙርለት።
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ መልሳችሁ ለመቀበል ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፤ በዚህም ወሮታችሁ ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።
ጳውሎስ ግን ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እኛ ሁላችን እዚሁ ስላለን፣ በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርስ!” ብሎ ጮኸ።
ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፤ ክፉ የሆነውን ሁሉ ተጸየፉ፤ በጎ ከሆነው ነገር ጋራ ተቈራኙ።
ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችንም የምንተናነጽበትን ማንኛውንም ጥረት እናድርግ።
ፍቅርን ተከታተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን፣ በተለይም ትንቢት የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ።
ጢሞቴዎስ ወደ እናንተ ከመጣ፣ ዐብሯችሁ ያለ ፍርሀት እንዲቀመጥ አድርጉ፤ እርሱም እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና።
እንግዲህ በመካከላችሁ መካሰስ መኖሩ ራሱ ውድቀታችሁን ያሳያል። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን?
ስለዚህ ዕድሉ ካለን ለሰው ሁሉ፣ በተለይም ለእምነት ቤተ ሰቦች መልካም እናድርግ።
እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ።
ሆኖም ከእናንተ እያንዳንዱ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባሏን ታክብር።
በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ የጽድቅ ፍርድን ብቻ ተከተል።
ወደ መንግሥቱና ወደ ክብሩ ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትኖሩ ዘንድ አበረታታናችሁ፤ አጽናናናችሁ፤ አጥብቀንም ለመንናችሁ።
ነገር ግን ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ፤
የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን ተከታተል።
የጌታም ባሪያ ሊጣላ አይገባውም፤ ይልቁን ለሰው ሁሉ ገር፣ ለማስተማር ብቃት ያለው፣ ትዕግሥተኛም መሆን ይገባዋል፤
እንዲሁም በማንም ላይ ክፉ እንዳይናገሩ፣ ሰላማውያን እንዲሆኑ፣ ለሰዎችም ሁሉ ከልብ የመነጨ ትሕትና እንዲያሳዩ አስገንዝባቸው።
ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ለመኖር የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ለመቀደስም ፈልጉ፤ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ማየት አይችልም።
እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን ስላነጻችሁ፣ ለወንድሞቻችሁ ቅን ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ።
ለሰው ሁሉ ተገቢውን አክብሮት ስጡ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።
ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች እያደረጋችሁ በረከትን ለመውረስ ነው።
ወዳጅ ሆይ፤ መልካም የሆነውን እንጂ ክፉውን አትምሰል። መልካም የሆነውን የሚያደርግ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። ክፉ የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።
እኔም ልሰግድለት በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ እርሱ ግን፣ “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክር ከያዙት ወንድሞችህ ጋራ አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና” አለኝ።
እርሱ ግን፣ “ተው፤ ይህን አታድርግ እኔ ከአንተና ከወንድሞችህ ከነቢያት እንዲሁም የዚህን መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁት ሁሉ ጋራ አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ” አለኝ።
በጥንት አባባል፣ ‘ከክፉ አድራጊዎች ክፉ ድርጊት ይወጣል’ እንደ ተባለ፤ አሁንም እጄ በአንተ ላይ አትሆንም።