አገልጋዩ፣ “እኔ የአንድ ሰቅል ጥሬ ብር ሩብ አለኝ፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረን ዘንድ ገንዘቡን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ” ሲል በድጋሚ መለሰለት።
ንጉሡም የእግዚአብሔርን ሰው፣ “ዐብረኸኝ ወደ ቤት እንሂድ፤ አንድ ነገር ቅመስ፤ ስጦታም አደርግልሃለሁ” አለው።
ስትሄጂም ዐሥር እንጀራ፣ ጥቂት ሙልሙል ዳቦ እና አንድ እንስራ ማር ይዘሽ ሂጂ፤ እርሱም በልጁ ላይ የሚደርሰውን ይነግርሻል።”
አገልጋዩ ግን፣ “እነሆ፤ በዚህች ከተማ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ፤ እርሱም በጣም የተከበረ ነው፤ የሚናገረውም ሁሉ በትክክል ይፈጸማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረን ይሆናልና ወደዚያ እንሂድ” ሲል መለሰለት።