ሳኦልም በቅጥሩ በር ላይ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፣ “የባለራእዩ ቤት የት እንደ ሆነ ትነግረኛለህ?” ሲል ጠየቀው።
ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ እግዚአብሔር፣ “ያ የነገርሁህ ሰው እነሆ፤ እርሱም ሕዝቤን ይገዛል” አለው።
ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ባለራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋራ ስለምትበሉ ከፊቴ ቀድማችሁ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ውጡ፤ ነገ ጧት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህ ያለውንም እነግርሃለሁ።