ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሙሉ ተጓዙ፤ የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከቤትሳን ግንብ ላይ አውርደው ወደ ኢያቢስ አምጥተው አቃጠሉ።
ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።
በዳዊት ከተማ ከዐለት አስፈልፍሎ ለራሱ ባሠራውም መቃብር ቀበሩት። በቅመማ ቅመምና በልዩ ልዩ ጣፋጭ ሽቱዎች በተሞላ ቃሬዛ ላይ አኖሩት፤ ስለ ክብሩም ትልቅ እሳት አነደዱ።
በሰላም ትሞታለህ። ሕዝቡ ከአንተ በፊት ለነበሩት ነገሥታት አባቶችህ ክብር በቀብራቸው ጊዜ እሳት እንዳነደዱ፣ በቀብርህም ጊዜ ስለ ክብርህ እሳት ያነድዳሉ፤ “ዋይ ዋይ ጌታችን!” እያሉም ያለቅሱልሃል፤ እኔ ራሴ ይህን ቃል ተናግሬአለሁና፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ”
በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋራ የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል።
የጦር መሣሪያውን በአስታሮት ቤተ ጣዖት ውስጥ አስቀመጡት፤ ሬሳውን ደግሞ በቤትሳን ግንብ ላይ አንጠለጠሉት።