ወደ ዔሊም ሮጦ በመሄድ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው። ዔሊ ግን፣ “እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው፤ እርሱም ሄዶ ተኛ።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ጠራው። ሳሙኤልም፣ “እነሆኝ” አለ፤
ደግሞም እግዚአብሔር፣ “ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሣና ወደ ዔሊ ሄዶ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው። ዔሊም መልሶ፣ “ልጄ ሆይ፤ እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው።