ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአንኩስ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተ ሰቡ ጋራ ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋራ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢግያ ጋራ ነበር።
እንዲሁም ዳዊት ዐብረውት የነበሩትን ሰዎች ከነቤተ ሰቦቻቸው አመጣቸው፤ እነርሱም በኬብሮን ከተሞች ተቀመጡ።
የሰውየው ስም ናባል፣ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር።
ሳኦልም፣ ዳዊት ወደ ጋት እንደ ሸሸ በሰማ ጊዜ፣ እርሱን ማሳደዱን ተወ።
ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ እንደ ደረሱም፣ እነሆ፤ ከተማዪቱ በእሳት ጋይታ፣ ሚስቶቻቸው፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ተማርከው አገኙ።
ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያም ተማርከው ነበር።