ለሰዎቹም፣ “እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ከማድረግና እግዚአብሔር የቀባው ስለ ሆነም እጄን በርሱ ላይ ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ” አላቸው።
ዳዊትም፣ “ታዲያ እግዚአብሔር የቀባውን ለማጥፋት እጅህን ስታነሣ እንዴት አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው።
ዳዊት ተዋጊዎቹን ከቈጠረ በኋላ ኅሊናው ስለ ወቀሠው፣ “ባደረግሁት ነገር ታላቅ ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል እንድታርቅ እለምንሃለሁ፤ የፈጸምሁት ታላቅ የስንፍና ሥራ ነውና” አለ።
ናቡቴ ግን አክዓብን፣ “ዐፅመ ርስቴን እለቅቅልህ ዘንድ እግዚአብሔር አይበለው” ሲል መለሰለት።
እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ፤
የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ።
ማንም በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁልጊዜ መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጕቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”
ዳዊት ሰዎቹን በዚህ ቃል ገሠጻቸው፤ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ከዋሻው ወጥቶ ሄደ።