Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ሳሙኤል 24:2

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺሕ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዐለት” ወደተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤

“የበረሓ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋሊያ ስታምጥስ ተከታትለህ አይተሃል?

ረዣዥሙ ተራራ የዋሊያ መኖሪያ፣ የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው።

ሹማምንታቸው ከገደል አፋፍ ቍልቍል ይወረወራሉ፤ ቃሌ የምታረካ ናትና ይሰሟታል።

ክፉዎች ጻድቁን ይከታተሉታል፤ ሊገድሉትም ይሻሉ።

ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤ ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ።

ሳኦል ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋራ፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋራ ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።

ከዚያም ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ፣ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሊዋጋ ሄደ። ከዚህ የተነሣም የዚያን ቦታ ስም ሐማለኮዝ ብለው ጠሩት።

ስለዚህ ሳኦል ተነሣ፤ ከእስራኤል የተመረጡትን ሦስት ሺሕ ሰዎችን ይዞ፣ ዳዊትን ፍለጋ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች