Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ሳሙኤል 23:28

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ፣ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሊዋጋ ሄደ። ከዚህ የተነሣም የዚያን ቦታ ስም ሐማለኮዝ ብለው ጠሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፍሳችን እንደ ወፍ፣ ከዐዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም አመለጥን።

ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትን ሊፈልጉት ሄዱ፤ እርሱም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ወደ ዐለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ። ሳኦልም ይህን እንደ ሰማ፣ ዳዊትን በማሳደድ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ዘልቆ ገባ።

አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፣ “ፍልስጥኤማውያን አገሩን ወረውታልና ቶሎ ድረስ!” አለው።

ዳዊትም ከዚያ ወደ ላይ ወጥቶ በዓይንጋዲ ምሽጎች ተቀመጠ።

ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ከተመለሰ በኋላ፣ “እነሆ፤ ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገሩት።

ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺሕ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዐለት” ወደተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች